Error message

Deprecated function: Array and string offset access syntax with curly braces is deprecated in include_once() (line 1389 of C:\xampp\htdocs\tourism\includes\bootstrap.inc).

የደቡብ ክልል ህልና ቱሪዝም ቢሮ፣የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ  ቢሮ እና ደንና  አከባቢ ጥበቃ ቢሮ 15ኛው የሰንደቅ ዓለማ ቀን በድምቀት ተከበረ
‹‹ሰንደቅ ዓለማችን የብዝሀነታችን መገለጫ የሉዓለዊነታችን  መሶሶ ነው›› በሚል መሪ ቃል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ፣የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና  ደንና  አከባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊችና  ሰራተኞች 15ኛውን የሰንደቅ ዓለማ ቀን በዓል በመስሪያ ቤታችን ቅጥር ግቢ ውስጥ ድምቀት  ተከበረ፡፡
በበዓሉ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ በመልዕክታቸው የሰንደቅ ዓለማ ቀን በዓል የአንድነታችን እና የሉዓለዊነታችን መገለጫ መሆኑን ጠቅሰው በአንጻሩም ለልማት ፣ለመልካም አስተዳደር እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ሰንደቅ ዓለማችን ለጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ ዋስትና ፣የመቻቸልና አብሮነታችን መገለጫ እንዲሁም  ፈተናዎችን በአንድነት መክተን የሚንሸጋገርበት መሸጋገሪያችን ነው ብለዋል፡፡
በበዓሉ የሰንደቅ ዓለማ ሥነ-ሥርዓት ላይ  የአትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር ተዘምሮ የፕሮግራሙ መጠቃለያ መደረጉን ጠቅሶ  የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

 

Leave a comment

Filtered HTML

  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <blockquote> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd>
  • Lines and paragraphs break automatically.

Plain text

  • No HTML tags allowed.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Lines and paragraphs break automatically.