Error message

Deprecated function: Array and string offset access syntax with curly braces is deprecated in include_once() (line 1389 of C:\xampp\htdocs\tourism\includes\bootstrap.inc).

የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር 3ኛውን ክልል አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባኤ ባካሄደበት ወቅት የምርምር ውጤቶች አካል የሆኑትን የተለያዩ የክልሉን ብሔረሰቦች ባህል፣ቋንቋ፣ታርክ እና ቅርስ የሚያንጸባርቁ ምሳሌያዊ አነጋገሮች፣ተረቶች፣እንቆቅልሾች እና ሌሎች ታርካዊ፣ባህላዊ እና ተፈጥሮአዊ ዕሴቶችን የያዙ መጻህፍት ምረቃ እና በጥናትና ምርምሩ ስራ ለተሳተፉ አካላት የእውቅና አሰጣጥ መርሃግብር አካሂዷል።
በመድረኩ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን ከነዚህም የቦዲ እና የበና ብሔረሰቦችን ባህልና ታሪክ የሚያትት ጥናታዊ ጽሑፍ፣ተረት የማስተማር ሚና በሚል የተዘጋጀ አጭር ዳሰሳ ፣ እንዲሁም የባህል ኢንደስትሪ ለኢኮኖሚ ልማትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያለው ምቹ ሁኔታ በሚል የተዘጋጀ የዳሰሳ ጥናት እና በሌላ የተዘጋጁ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩ የተሳተፉት ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉድሼ፣የዩኒቨርሲቲው የማናጅመንት አባላት፣በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ተወካዮች እንዲሁም የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ፣ ም/ል ቢሮ ኃላፊዎችን ጨምሮ ዳይሬክቶሬቶች፣ከፍተኛ ባለሙያዎች፣የተለያዩ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ባህልና ቱሪዝም መምሪያና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች በጂንካ ከተማ በድምቀት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ ይህ የጥናትና ምርምር ጉባኤና የመጻህፍት ምረቃ ፕሮግራም በዘርፉ  ላይ ለተሳተፉ አካላት የሚሰጠው የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር፣ተሳታፊዎችን ለላቀ ሥራ የሚያነሳሳ መሆኑን ጠቅሰው በዕለቱ የሚቀርቡ ጥናታዊ ጽሑፎችና ከተሳታፊዎች የሚሰጠው አስተያየት ቀጣይ ተቋሙ ለሚሰራው ተግባር ትልቅ ግብዓት ከመሆኑም በላይ የባህልና ቱሪዝም ሥራዎችን ይበልጥ ለማልማትና ለመጠበቅ እንዲሁም ከዘርፉ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ስኬት የሁሉ ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት አስፈላጊ መሆኑን ተናግሯዋል፡፡
አያይዘውም አሁን ላይ መንግስት ትኩረት እያደረገ ከለው ዘርፎች አንዱ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ አንዱ በመሆኑ ዘርፉን በማልማት ውጤታማነትን በማረጋገጥ ህብረተሰቡ ጥቅም እንዲያገኝ ለማድረግ በየደረጃው ያለን ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በመድረኩ የተለያዩ መወያያ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን ከእዚህም መካከል በጂንካ ዩኒቨርሲቲ መምህርት ሀይማኖት አለማየሁ በቦዲ እና በና ብሄረሰቦች ባህልና ታረክ ጥናታዊ ጽሁፍ፣አቶ ግርማ ቡኬ ተረት የማስተማር ሚና አጭር ዳሰሳ በሚሉ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረጉ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ተሳታፊዎችም በበኩላቸዉ የጥናትና ምርምር ሥራዎች የሕዝቡን ችግር ፈቺ መሆን እንዳለባቸዉ እንዲሁም ትኩረት ያልተሰጡ የተለያዩ ብሄረሰቦች ቋንቋ፣ባህል እና ታሪክ ማልማትና ሌሎችን የክልሉን ብሄረሰቦች መልካም ዕሴቶችን ልምድና ተሞክሮ በማስፋት የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር የባህል ሥራዎችንና ዉጤቶችን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ይገባል የሚሉ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆኑ የቱሪዝም ዘርፍ በተመለከተ የቱሪስት መዳረሻዎችን ከማልማት አንጻር ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የገለጹት ተሳታፊዎቹ  ከክልል ጀምሮ በተዋረድ ተቀራርቦ በመስራት ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገለግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤሊያስ አለሙ እና የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ መልካም ዕሴቶችን በማሳደግ ለልማት ፤ለመልካም አስተዳደር፤ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ፋይዳ የጎላ በመሆኑ በጉድለቶች ላይ በትኩረት በመሥራት ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ በማስፋት የባህልና ቱሪዝም ሥራዎች ዉጤታማ ለማድረግ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጽንኦት መሰጠት እንዳለበት መናገራቸዉን የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡
ትግስቱ ገዕናሞ
 
 

Leave a comment

Filtered HTML

  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Allowed HTML tags: <a> <em> <strong> <cite> <blockquote> <code> <ul> <ol> <li> <dl> <dt> <dd>
  • Lines and paragraphs break automatically.

Plain text

  • No HTML tags allowed.
  • Web page addresses and e-mail addresses turn into links automatically.
  • Lines and paragraphs break automatically.